እንኳን ወደ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ዲጂታል አገልግሎት በደህና መጡ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን በዘመናዊ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመን፣ ለተገልጋዮች ፈጣን፣ ምቹ፣ ጊዜ ቆጣቢ እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት ይህን የዲጂታል አገልግሎት አዘጋጅቷል። ይህ ዲጂታል ስርዓት የቢሮውን ዋና ዋና አገልግሎቶች በመረጃ ቴክኖሎጂ በተደገፈ መልኩ እንዲደርሱ ያደርጋል። ተገልጋዮች የፈቃድ መረጃዎችን መመልከት፣ ማረጋገጥ እና የአገልግሎት ሁኔታን መከታተል በቀላሉ ይችላሉ። በዚህ ስርዓት መተግበር፣ የመረጃ ግልፅነት ይጠናከራል፣ የአገልግሎት ፍጥነት ይጨምራል። ቢሮው በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት በማቅረብ ተገልጋዮችን በዘመናዊ እና ተስማሚ መንገድ ለማገልገል የሚያግዝ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት ነው።

የተገልጋዩን ሙሉ መረጃ በአንድ ስማርት/ዲጂታል ካርድ ማደራጀት

ይህ የዲጅታል አገልግሎት የተገልጋዩን ሙሉ መረጃ በአንድ ዲጂታል/ስማርት ካርድ በማደራጀት ያቀርባል። ተገልጋዮች የፈቃድ መረጃዎችን መመልከት፣ ማረጋገጥ እና የአገልግሎት ሁኔታን መከታተል በቀላሉ ይችላሉ። ይህ አገልግሎት የቢሮውን አሰራር ከማዘምን በተጨመሪም የተገልጋዩንም ሆነ የአገልግሎት ሰጭውን አሰራር ያቀለጥፋል።

ለእያንዳንዱ ካርድ የራሱ የሆን ፈጣን ምላሽ ኮድ (Quick Response Code) ማዘጋጀት

ለሁሉም ተገልጋይ እያንዳንዱ ካርድ የራሱ የሆን ፈጣን ምላሽ ኮድ (Quick Response Code) QR Code ይዘጋጃል። ይህፈጣን ምላሽ ኮድ (Quick Response Code) የተገልጋዩን ሙሉ መረጃ የያዘ እና ህጋዊነቱን ማረጋገጫ ነው።

ለእያንዳንዱ ካርድ የራሱ የሆን የፋይል ቁጥር ማረጋገጫ Barcode ያለው።

ይህ Barcode ተገልጋዩን ሆነ አገልግሎት ሰጭውን ፋይል በመፈለግ የሚያጠፋውን ጊዜ እና እንግልት የሚቀንስ ነው። በስማርት ካርዱ ላይ ያለውን የbarcod Scan በማድረግ የተገልክጋዩን ፋይል በቀላል መንገድ ማገኘት ይችላሉ።

የተደራጀ የመረጃ አያያዝ የሚያገኙበት

ቢሮው ምቹ አገልግሎተ ለመስጠተ እንዲያስችል ሙሉ ፋይል የራሱ Barcode እና QR CODE ተዘጋጅቶለት በተጨማሪም የፋይል ቁጥር ተስጥቶት በተመደበለት ቦታ ይቀመጣል። ይህም ፋይል ለመፈለግ የሚወስደውን ጊዜ እና ድካም ይቀንሳል። በስማርት ካርዱ ላይ ያለውን የbarcod Scan በማድረግ የተገልጋዩን ፋይል በቀላል መንገድ ማገኘት ይችላሉ።

ስለ አልሚው የተደራጀ መረጃ እና የሰራተኛ ማስረጃ በንድ ካርድ የሚያገኙበት

በዚህ አገልግሎት ብክልሉ ተንቀሳቅሰው የሚሰሩ አልሚ ባለሃብቶች እና ሰራትኞች ሙሉ መረጃ እና ማስረጃዎችን ያካተት በአንድ ስማርት ካርድ የሚያገኑበት ነው። ይህም የአልሚውን ህጋዊ የማልማት ፍቃድ እናዳለው ማረጋገጫ ሆኖ ሊወሰድ ይችላል።

ጥብቅ ሴኩሪቲ ያለው የመረጃ አያይዝ ስረአት የሚያገኙበት

ይህ አገልግሎት የመረጃ አያያዝ ስረአት በጥብቅ ሴኩሪቲ የተደገፈ መልኩ የተገልጋዩን መረጃዎችን እና ፋይሎችን የሚይዝ ነው። ከዚህ በፊት የነበረ የፋይል መጥፋት እና መበላሽት በሰፊው የሚቀርፍ አገልግሎት ነው።

ሃላፊዎች

የቢሮ ኃላፊዎች መረጃ

አቶ አሻድሊ ሀሰን

ርዕሰ መስተዳድር

ቱጃኒ አደም

ቢሮ ሀላፊ

ናስር ሙሃመድ

ም/ቢሮ ሀላፊ